Lirik Lagu Tekebel Getish Mamo
እንደው መላ: መላ: መላው ሳይጠፋሽ
ኣየሁሽ ለፍቅርኣየሁሽ ለፍቅር ግራ ሲገባሽ
ሲታውቂው መንገዱን የፍቅርን ጎደና
ግራ መጋባትሽ አይመስልም የደና
መላዬ የሆነው ይሁን ብዬ ደሞ እንዳልወድሽ
መላዬ እንኳ ለኔ ቀርቶ አንቺም ለራስሽ
አትበጂውምና ፍቅር ካነሰሽ
እንደው ምን ላድርግሽ
ለማማር ለማማር ለቁንጅናሽ ዳሩ
ሚወጣለት የለም እማኝሽ ባገሩ
እንደው ልብሽ እንጂ ልብ እልል ያለው
ፍቅር አልገባ ብሎት ሰው የታዘበው
ከማድጋ ውሀ ቀድተሽ በጣሳው
መስጠት ታውቂ ነበር ለተጠማ ሰው
ምነው ዛሬ ታድያ ሲደርሽ የልብሽ
ሁሉን ለኔ: ለኔ: ለኔ ማለትሽ
ችሎ: ችሎ: ችሎ ሲበቃው
ላይመለስ በቀላሉ ሰው
መቻል: መቻል: መቻል ምንድነው
መተው እንጂ ከሰው ሚያኖረው
ኸረ ነይይይይይይይ
ኸረ ነይ
ኸረ ነይ ኸረ ነይ
ኸረ ነይ ኸረ ነይ
ሆዴ የኔ አበባ
ዘመድዬ እንዴት ነሽ?
አካሌ እንደምነሽ? (ተቀበል ተቀበል)
ሆዴ የኔ አበባ
አሞሽ አልሰማሁኝ እግዚሄር ይማርሽ
(ድገመው)
አሞሽ አልሰማሁኝ እግዚሄር ይማርሽ
አንቺ ሰው አታጪም የሚያስታምምሽ
የሚያስታምምሽ
ቻይው ይተውሻል
ባንቺ ብቻ አይደለም
(ድገመው)
አይዞሽ ይተውሻል ባንቺ ብቻ አይደለም
ዘንድሮ ያልተነካ ያልታመመ የለም
ያልተመመ የለም
አንቺ ባለጊዜ ሆነሽ ባለቀን
(ድገመው)
አንቺ ባለጊዜ ሆነሽ ባለቀን
እንዳንወቃቀስ
እንዳንሆን ሆነን
እንዳንሆን ሆነን
ይኸው ዛሬ ድረስ ኖረነው ኖረነው
(ድገመው እስቲ)
ይኸው ዛሬ ድረስ ኖረነው ኖረነው
ቀን እየተቆጣን ዝም ማይል ማነው
ዝም ማይል ማነው
አንቺም አባወራ: እኔም አባወራ
አንቺም አባወራ: እኔም አባወራ
ግራ ገባው ቤቱ በማን እንደሚጠራ
በማን እንደሚጠራ
አንቺ እጅስ ሰፊ ነው የለም ሚጎድልሽ
አንቺ እጅስ ሰፊ ነው የለም ሚጎድልሽ
ለኔ ህልም እንጀራ ወግ እየጋገርሽ
ወግ እየጋገርሽ
ሂሳብ አለብኝ እንዴ?
ተከፍሏል
አመስግናለው እንግዲህ
post a comment